D
Posted by Diredawa Prosperity Party
Aug 05, 2026 15 views 0 Comments

በኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተመራ ልዑካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

#DGC 6/2018

ልዑኩ ከአስተዳደሩ ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም ከድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ጋር በጋራ በመሆን የችግኝ ተከላውን አከናውኗል።

በዘንድሮው የክረምት ወቅት በበጎ ፈቃድ ሥራ ላይ በድሬዳዋ ችግኞችን በመትከልና የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖራቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ገልጸዋል።

አያይዘውም ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከተጀመረ በኋላ ሀገሪቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋኑን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አመላክተዋል።

ይህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የከርሰ ምድር ውሃን ለማበልጸግ ተጨባጭና ታሪካዊ ውጤቶች እያስመዘገበ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሯ ሰላማዊት ዳዊት በንግግራቸው በሰፊው ገልጸዋል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ማህበረሰቡ ችግኝ መትከልን ብቻ ሳይሆን የመንከባከብን ጥቅም በሚገባ ተረድቶ ዕለታዊ ተግባሩ ማድረጉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ፦ አገኘሁ ሸዋረጋ

Comments (0)

Be the first to share your thoughts.

Leave a Comment

Your email will not be published. Required fields are marked *